13 Episodes
6 Ratings
2021 First episode About KALANDRAS ካላንድራስ የአማርኛ ፖድካስት (RADIO) ነው:: ቃሉም ደግሞ አማርኛ [ካለ አንድ ራስ] እንደማለት የሚኾን
ነጻ ሃሳቦችን የምናንሸራሽርበት የኢንተርኔት ራዲዮ ሲሆን ማህበረሰብ ፣ ባህል ፣ ህግ ፣ ሃይማኖት . . . የማንነካው አይነኬ ፣ የማንዳሠው ጓዳ ጎድጓዳ ፣ የማንፈነቅለው የሃሳብ ድንጋይ አይኖርም።
ከወደዳችሁት እያዳመጣችሁ ባላችሁበት መተግበሪያ ላይ Rate በመስጠት እና Review በመጻፍ ብታግዙኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው።
Hosted by: Miki MAC
Publisher ካላንድራስ
Category society & culture
Language am
Explicit No
First episode 18 Dec 2021
Latest episode 3 Oct 2023 Latest episodes 13 episodes in the feed.
3 Oct 2023
Episode 12 : ቃልኪዳን ታደሰ - ክፍል 2 ቃልኪዳን ታደሰ በሙያዋ አርኪቴክትና የኢንቴሪየር ዲዛይን ባለሙያ ስትሆን ከካላንድራስ ጋር በነበራት የመጀመሪያው ክፍል ቆይታችን በህይወት ዘመኗ ስለገጠሙዋት ሁነቶች፣ ስለ ህይወት ተሞክሮዋ እንዲሁም ስለቤተሰቦቿና ልጅነቷ እየተጨዋወትን ውብ ቆይታ አድርገናል። ከቃልኪዳን ጋር የነበረን ቆይታ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሲሆን ብዙ ረብ ያላቸው ቁም ነገሮችን ከዳሰስንበት ዘለግ ያለ ጭውውታችን ስለስራዋና ከስራዋ ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ያወጋንበት ሁለተኛው ክፍል እነሆ።
ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify, Apple podcast, Google podcast, Teraki Appን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ።
3 Oct 2023
Episode 11 : ቃልኪዳን ታደሰ - ክፍል 1 ቃልኪዳን ታደሰ በሙያዋ አርኪቴክትና የኢንቴሪየር ዲዛይን ባለሙያ ስትሆን በህይወት ዘመኗ ስለገጠሙዋት ሁነቶች፣ ስለ ህይወት ተሞክሮዋ እንዲሁም ስለቤተሰቦቿና ልጅነቷ እየተጨዋወትን ውብ ቆይታ አድርገናል። ከቃልኪዳን ጋር የነበረን ቆይታ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሲሆን ብዙ ረብ ያላቸው ቁም ነገሮችን የዳሰስንበት ዘለግ ያለው ጭውውታችን የመጀመሪያውን በዚህ ክፍል ቀጣዩን ደግሞ በሚቀጥለው ክፍል ይዘንላችሁ የምንቀርብ ይሆናል።
ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify, Apple podcast, Google podcast, Teraki Appን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ።
5 Jul 2022
Episode 10 : የፍላጎት ተዋረድ እና የሰው ልጅ ባህርይ (ከሔኖክ ጋር) ይህ የዛሬው ክፍል የካላንድራስ ፖድካስት 10ኛው ክፍል ሲሆን የዚህ ሲዝን መጨረሻም በዚሁ የሚጠናቀቅ ይሆናል። በምእራፍ ሁለት ደግሞ እንደተለመደው ከሁሉም አይነት የሃሳብ ዘለላዎች የተጠጉ ጥሩ ጥሩ ክፍሎችን ይዤላችሁ በቅርቡ ተመልሼ እመጣለሁ። እስከዚያው ግን መቆያ ይሆናችሁ ዘንድ የዩትዩብ ቻናሌ Mikimac Views (https://www.youtube.com/c/MikiMacViews) ላይ በመሄድ በአይነታቸው ትንሽ ለየት ያሉና አጫጭር ቆይታ ያላቸውን ቪዲዮዎቼን እንድትመለከቱ በተጨማሪም SUBSCRIBE (https://www.youtube.com/c/MikiMacViews) በማድረግ እንደሁልጊዜውም የስራዬ አጋር እና አበርቺ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ።
ወደዛሬው የካላንድራስ ክፍል ስንገባ ስለአሜሪካዊው የስነ ልቦና ባለሙያ Abraham Maslow (https://en.wikipedia.org/wiki/Abraham_Maslow) (አብርሃም ማስሎው) Hierarchy of needs ስለተባለው ቲዮሪው እየተጨዋወትን ቆይታ የምናደርግ ይሆናል። በዚህ የካላንድራስ ክፍል ላይም እንደሁልጊዜው እንግዳ ይዤላችሁ መጥቻለሁ። እንግዳችን ሄኖክ ይባላል።
ኤርትራዊ ሲሆን በአሁን ወቅት ነዋሪነቱ በአሜሪካን ሃገር ነው። የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው በባዮ ኬሚስትሪ የትምህርት ዘርፍ ሲሆን የዶክትሬት ዲግሪውን ደግሞ በፋርማሲ ትምህርት አግኝቷል። ሄኖክ ከትምህርቱ ባሻገር በስነልቦና እና የሰው ልጅ ባህርይ ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች እና ትምህርቶች ቀልቡን እንደሚስቡትና ስለነዚሁ ጉዳዮች ከሰዎች ጋር መወያየት ፣ መጽሃፍትን ማንበብና ፣ ሰርክ አዳዲስ ተያያሽነት ያላቸው ሃሳቦችን መፈለግና ማወቅ ዝንባሌው ነው። ታዲይ ለዛሬም በዚሁ ጉዳይ ላይ የማስሎውን Hierarchy of needs theory ዘርዘር ባለ መልኩ እያጫወተን የሚቆይ የካላንድራስ (https://mikimac.org/kalandras) እንግዳችን ነው።
1 May 2022
Episode 9 : ሌላ ሰው - አዲስ መንገድ (Aida Abdella) የካላንድራስ ክፍል 9 እንግዳችን አይዳ አብደላ ነች። በመኖር ውስጥ ስለገጠማት አንድ ትልቅ የህይወት መልክ ቀያሪ ክስተት ታጫውተናለች። የአይዳ ታሪክ ለብዙዎቻችን አስተማሪ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም። በታሪኳ ውስጥ ስላለው ጭብጥ እና አንቂ ቁምነገር መናገር ታሪኩን እንዳያበላሸው በሚል ስጋት ብዙ ዝርዝር ውስጥ አልገባም።
ይህንን ክፍል አዳምጣችሁ ስታበቁ እንደተለመደው አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ብትልኩልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው። ካላንድራስን ከወደዳችሁት እና ሌሎች በርካቶች ቢሰሙት የሚበጅ ነው የምትሉ ከሆነ ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ወይም ሼር በማድረግ እንዲሁም እና spotify (https://open.spotify.com/show/3r8jwrTVTyPKPZdU5X38h1?si=15bbd442949a4780), Apple podcast (https://podcasts.apple.com/mt/podcast/kalandras/id1601534490), Google podcast (https://podcasts.google.com/feed/aHR0cHM6Ly9hbmNob3IuZm0vcy80ZTE0NWJlYy9wb2RjYXN0L3Jzcw), Teraki App (https://terakiapp.page.link/TK_DYN_SHARE?TK_DYN_SHARE_PODCAST=Kf476pKAfHhwdvqoflsu&_imcp=1)ን ተጠቅማችሁ የምታዳምጡ ከሆነ RATE በማድረግ እና REVIEW በመጻፍ ልታግዙኝ ትችላላችሁ።
12 Apr 2022
Episode 8: ስንት አየሁ? 🤔 / Sintayehu በዚህ የካላንድራስ ክፍል ከኢትዮጵያ ኬንያ ከኬንያ ደግሞ እስከ አሜሪካን ሃገር ድረስ የዘለቀና በብዙ የህይወት መልክና ውጣ ውረዶች የተፈተነ ድንቅ የቤተሰብ ታሪክ እንዳሥሣለን። ስደት ፣ ጥንካሬ ፣ ፅናት ፣ በፈተናዎች ያልወደቀ የቤተሰብ ፍቅር ፣ እምነት ፣ ስኬት . . . ብዙ ብዙ ቁምነገሮችን እንማርበታለን ብዬ አስባለሁ።
እንደተለመደው ሃሳብና አስተያየታችሁን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን Instagram (//www.instagram.com/kalandras_podcast) እና Telegram (//t.me/thisiskalandras) ላይ ልትልኩልን ትችላላችሁ።
ይህን ፖድካስት ከወደዳችሁት የምትሰሙበት መተግበሪያ ላይ Rate ብታደርጉልን ምስጋናችን የላቀ ነው።
For more info about Kalandras
www.mikimac.org/kalandras (//www.mikimac.org/kalandras)
31 Mar 2022
EPISODE 7 : ኢትዮጵያዊነት / Being Ethiopian? ኢትዮጵያዊነት ማለት ምንድነው?
የኢትዮጵያዊነት ፍቺ ወይም ትርጓሜ እንደያንዳንዳችን የህይወት ትርጓሜና ተሞክሮ የሚወሰን ነው።
አንድ መንገድ ላይ ሊስትሮ እየጠረገ ህይወቱን የሚመራ ልጅ፣ በወሲብ ንግድ የምትኖር አንድ የቡና ቤት ሴት ፣ ስልጣን ላይ ያለ የተመቸው ባለጊዜ ፣ የሃገሩን ዳር ድንበር ለማስከበር ድንበርና ተጋድሎ ላይ ያለ የሃገር ወታደር ፣ የሚጠጣው ውሃ ማግኘት ታላቅ የህይወት ፈተና የሆነበት አንድ አርብቶ አደር ፣ የዝናቡን መዘግየት እያሰበ የጎተራው ባዶነት የሚያስጨንቀው ምስኪን ገበሬ ፣ ለሃገሬ የሚጠቅም ሃሳብ አለኝ በማለቱ ከወህኒ የተጣለው ጋዜጠኝ ፣ የታክሲ የሚከፍለው ገንዘብ በማጣቱ በቀን ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በእግሩ እየተጓዘ የሚያስተምረው መምህር ፣ መሪ ነኝ ብለው ገዢ የሆኑና ዘውዱን የጨበጡ እለት ቃላቸውን ቅርጥፍ አድርገው የበሉ ጥጋበኞች በፈጠሩት ጸብ ህይወቱ እየተመሰቃቀለ ያለ የአንድ አካባቢ ህዝብ . . .
እነዚህ ሁሉ እንደጉራማይሌነታቸው ኢትዮጵያዊነትን የሚረዱበት መንገድም ብዙዎቻችን እንግዳ ተቀባይ ፣ የሰው ዘር መገኛ ፣ ሃይማኖተኛ ፣ ወ.ዘ.ተ . . . ከምንለው በእጅጉ የተለየ ነው።
የዚህ የፖድካስት ክፍል አላማም መስማማት ላይ እንድንደርስ ወይም ለቃሉ ፍቺ የሚሆን ሃሳብ ላይ ተስማምተን እንድንለያይ ሳይሆን እስከዛሬ ይዘን የመጣነውን እውነት እንድንሞግትና የውስጥ ጥያቄዎቻችንን አውጥተን እንድንወያይበት ታሳቢ በማድረግ የቀረበ ነው::
ሃሳብ አስተያየታችሁን ላኩልን።
Follow us on INSTAGRAM (//www.instagram.com/kalandras_podcast) and TELEGRAM (//t.me/thisiskalandras)
7 Mar 2022
EPISODE 6 : ቆይታ ከገጣሚ ዮሐንስ ሞላ ጋር ዮሐንስ ሞላ "የብርሃን ልክፍት" እና "የብርሃን ሰበዞች" የተሰኙ ሁለት የግጥም መጽሃፍትን ያሳተመ ገጣሚ ሲሆን በዚህ 6ኛው የካላንድራስ ፖድካስት ክፍል የተለያዩ ጉራማይሌ ሃሳቦችን እያነሳን የተጨዋወትንበትን ቆይታ እነሆ!!
ሃገር ፣ ማንነት ፣ ሞት ፣ ፍቅር ፣ ገንዘብ . . . በርከት ያሉ ሃሳቦችን እንዳሥሣለን።
⚠️በዚህ ፖድካስት ላይ "የብርሃን ቀለማት" በሚል የተጠቀሰው አንደኛው የዮሐንስ ሞላ መፅሃፍ ርእስ በስህተት ሲሆን "የብርሃን ሰበዞች" በሚል እንዲታረም እንጠይቃለን::
ከታላቅ ይቅርታ ጋር 💛🙏
13 Feb 2022
Episode 5 : Feminism? 🤔 ሴት ልጅን ለማክበርና የሚገባትን ሁሉ ታገኝ ዘንድ የአቅማችንን ሁሉ መጣር አለብን። ይህ ደግሞ ሰበብና ምክንያት አይፈልግም። ሴት እናት ፣ እህት ፣ ሚስት ፣ ሃገር . . . ስለሆነች ሳይሆን እንደኔ ፣ እንዳንተ ፣ እንደ እኛና እንደሁላችን ሰው ስለሆነች ብቻ . . .
28 Jan 2022
Episode 4 : ሃይማኖት (Religion - How we see it?) ሃይማኖት ምንድነው? እምነትስ እንደምን ያለ ነው? ጥቅምና ጉዳትስ ይኖራቸው ይሆን? በዛሬው የካላንድራስ ክፍል ሃይማኖትና እምነትን ፣ የሰዎችን የህይወት ልምምድ እና እይታ እንዳሥሣለን። ይህ ኢፒሶድ በClubhouse (https://www.clubhouse.com/club/kalandras-%E1%8A%AB%E1%88%8B%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%88%AB%E1%88%B5)የካላንድራስ ክፍል ከተደረገ የሰዓታት ውይይት ላይ ለፖድካስት እንዲያመች ተደርጎ ተመጥኖ የቀረበ ነው።
ካላንድራስን Rate ያድርጉ። ለወዳጆቻችሁ አጋሩልን። እጅግ ከላቀ ምስጋና ጋር።
ልዩ ምስጋና - ለትእግስት ሁሴን 💛💛💛
19 Jan 2022
Episode 3: ሰርፀ ፍሬስብሃት - የዚህ ዓለም ትርጉም ፤ የሰው ልጅ ሰርፀ ፍሬስብሃትን ብዙዎቻችን የምናውቀው በሙዚቃ ባለሙያነቱ ነው። ከሙዚቃው ባሻገር ለየት ያለ የህይወት መረዳት ካላቸው ሰዎችም አንዱ ነው። በዚህ Episode "የሰው ልጅ ፍጥረቱ እንደምን ያለ ነው?" በሚለው ዙሪያ ያደረግነውን ቆይታ እነሆ።
7 Jan 2022
Episode 2: በራስ መተማመን (Perspectives on self-confidence) በራስ መተማመንን እንዴት እንረዳዋለን? በራሴ እተማመናለሁ ለማለትስ መስፈርቶቹ ምን ይሆኑ? በራስ ከመተማመን ጋር ተያይዞ ያለንን መረዳት ከተለያዩ አንጻሮች ለመመልከት እንሞክራለን። በዚህ የፖድካስት ክፍል ላይ በራስ ስለመተማመን ሃሳባቸውን የሚያጋሩን ተሳታፊዎች ይኖሩናል። ይህ የፖድካስት ክፍል ክለብ ሃውስ ላይ ከተደረገ የ5 ሰዓታት ውይይት ላይ ለፖድካስት እንዲያመች ተመጥኖ የቀረበ ሲሆን ሙሉውን ውይይት ለማድመጥ የምትፈልጉ ከታች የተቀመጠው ሊንክ ላይ ታገኙታላችሁ።
https://www.clubhouse.com/room/xnbLQWd4
ካላንድራስን Rate ያድርጉ። ለወዳጆቻችሁ አጋሩልን። እጅግ ከላቀ ምስጋና ጋር።
ልዩ ምስጋና - ለትእግስት ሁሴን 💛💛💛
27 Dec 2021
Episode 1: ኢታና ዲሳሳ - ሰውነት (Being Human) ኢታና ነዋሪነቱ በአሜሪካን ሃገር የሆነ ጎበዝ ሙዚቀኛ ፣ የቤተ ክርስቲያን ዘማሪ እንዲሁም በስነ መለኮት ፣ ሂሳብ እና የቴክኖሎጂ ትምህርቶች የተጋ ኢትዮጵያዊ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ባለትዳር እና የ2 ልጆች አባት ነው።
ኢታና በካላንድራስ ስለህይወት አረዳዱ ፣ ስለቤተሰቦቹ ፣ ስለ privillege እና በህይወት ውስጥ ከሚገያጋጥሙ ልዩነቶች ጋር እንዴት እያመቻመቸ እንደሚያልፍ ያጫውተናል።
18 Dec 2021
ይህ ካላንድራስ ነው This is KALANDRAS. A vibecast
We share vibes, sharing what we know from eachother, breaking taboos, questioning society . . . BZU BZU
Reach and audience Public platform figures. Ratings count people who left a rating, not total listeners.
Apple Podcasts (US) 5.0 / 5 6 ratings Research this show Explore Pod Engine's podcast research tools and transcript access.
See plans Is this your podcast? Claim your show to manage its details on Pod Engine.
Claim KALANDRAS Where this data comes from Each source has its own observation date. These dates do not mean all data was checked at once.
RSS feed Last successful check: 24 Aug 2026 .
Apple Podcasts ratings (US) Snapshot recorded: 21 Oct 2026 .
Spotify ratings Snapshot recorded: Date unavailable. Host of KALANDRAS? Claim your podcast to manage its listing and keep your show details accurate.
Claim this podcast Pod Engine is an independent podcast discovery and analytics service and is not affiliated with or endorsed by this podcast. Artwork and show content belong to their owners. Full legal notice .
Explore this showPodcast research with Pod Engine
See plans